የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ለስራ ትብብር የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲን ጎበኙ፡፡ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ በዩኒቨርስቲው የስራ ትብብር ጉብኝት አድርገዋል፡፡ በዚህ ጉብኝት ላይም የትምህርት እና ስልጠና ፖሊሲዎች የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲን ልዩ ባህሪ ባማከለ መልኩ እንዲቀረፁ ሲሉ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኮማንዳንት ብ/ጀነራል ከበደ ረጋሳ ጠይቀዋል፡፡ Continue Reading