የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ  የስራ ጉብኝት አደረጉ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ለስራ ትብብር የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲን ጎበኙ፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ
በዩኒቨርስቲው የስራ ትብብር ጉብኝት አድርገዋል፡፡ በዚህ ጉብኝት ላይም የትምህርት እና ስልጠና ፖሊሲዎች የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲን ልዩ ባህሪ ባማከለ መልኩ እንዲቀረፁ ሲሉ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኮማንዳንት ብ/ጀነራል ከበደ ረጋሳ ጠይቀዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋም አንድ ሀገር በጠንካራ መሰረት ላይ ልትገነባቸው ከሚገቡ ተቋማት ተቀዳሚዎቹ የመከላከያ እና የትምህርት ተቋማት መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ በዚህም መሰረትም በቀጣይ በሚደረጉ የፖሊሲ ብሎም የመመሪያ ማሻሻያ እና ክለሳዎች ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲን ልዩ ባህሪን ባገናዘበ መልኩ እንዲተገበር ሚኒስቴር መስሪያቤታቸው የበኩሉን አስተዋጽዎ እንደሚያደርግ አስረድተዋል፡፡

ሚኒስትሩ አያይዘውም እንደ ሀገር ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገባው ተማሪ ቁጥር መቀነስ ጋር ተያይዞ ዩኒቨርሲቲው የተማሪ ቅበላ ቁጥር እጥረት እንዳይገጥመው ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ እንደሌሎቹ ዩኒቨርሲቲዎች የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲዎች ምርጫ ዝርዝር ውስጥ እንዲካተት እንደሚሰሩ አብራርተዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የሀገሪቱን መከላከያ ሰራዊት በእውቀት በማሳደግ ረገድ ለሚደረገው የትምህርት ጥራት ማሻሻያ እያሳየ ያለውን ድጋፍ አድንቀው፡፡ አሁንም ትብብር እና ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የዩኒቨርሲቲው ቦርድ አባል ዶ/ር ሰይፉ ጌታሁን ጠይቀዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የተለያዩ የኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ቤተ-ሙከራዎች እና የምርምር ማዕከላት ጉብኝት ተደርጓል፡፡

በጉብኝቱም የዩኒቨርሲቲው የቦርድ አባላት እና ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በቀጣይነት ትምህርት ሚኒስቴር በዩኑቨርሲቲው የትምህርት ጥራት ማሻሻያ እና ድጋፎች ላይ በትብብር እንደሚሰራ ተመላክቷል።

Related Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *