የመከላከያ ኒቨርሲቲ በቢሸፍቱ ከተማ በጎልባ ተራራ ላይ ‹‹ ነገን ዛሬ እንትከል ›› በሚል መርህ የችግኝ ተከላ ያካሄዴ ሲሆን በችግን ተከላው እለት የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ የሰራዊት አባላት ሲቪል ሰራተኞች እና ሲቪል ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን በእለቱም አስር ሽህ የሚሆን የተለያዩ ሀገር በቀል ችግኞችን በመትከል አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡
በችግኝ ተከላው ዕለት በመገኘት የችግኝ ተከላውን ያስጀመሩት የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ዋና አዛዥ ብ/ጀኔራል ከበዴ ረጋሳ ሲሆኑ ሀገራችን ኢትዮጲያ ከሃምሳ አመት በፊት ስልሳ በመቶ በደን የተሸፈነች ሀገር እንዴ ነበርች እና ራሳችን ያወደምናትን ሀገር እኛው በራሳችን መልሰን እንተክለዋለን በማለት ተናግረው ሰራዊቱ በሄደበት ቦታ ሁሉ የሚያርፍበትን በረሃ በአፈሰሰው ደም ላይ፤በተከሰከሰው አጥንቱ ላይ ችግኝ በመትከል ሀገሩን ለምለም በማድረግ የቆዬ ልምድ ያለው መሆኑን ተናግረው ይህንንም ልምድ መቀጠል አለበት በማለት አፅንኦት ሰጥተው ተናግረው በዕለቱ ተሳትፎ ላደረጉ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና ለአካባቢው ወጣቶች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በተጨማሪም በችግኝ ተከላው ወቅት በመገኘት ተሳትፎ ካደረጉ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መካከል የሀገሪቱን አየር ፀባይ ምቹ ለማድረግ ችግኝን መትከል ወሳኝ መሆኑን ተናግረው በዚህ ሀገርን እና ተፈጥሮዋን የመቀየር መርህ ላይ መሳተፍችን እድለኞች ነን በማለት በተመሳሳይ ሀሳባቸውን ገልፀዋል፡፡
በሰኢድ አሊ
ፎቶ ግራፈር
አማኑኤል ታደሰ