በሀገር አቀፍ ደረጃ “አረንጓዴ አሻራችን ለትውልዳችን” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ በሚገኘው 4ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ በመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ስር የሚገኙ ክፍሎች የኢንጅነሪንግ ኮሌጅ߹ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ߹የሪሶርስ ማኔጅመንት ኮሌጅ߹የምርምር ተቋም߹የዩኒቨርሲቲ ስታፍ ߹የዩኒቨርሲቲ ሲቪል ማህበረሰብ እንዲሁም የ93ኛ ክ/ጦር 6ኛ ሻለቃ የሰራዊት አባላት በጋራ በመሆን ሐምሌ 11/2014 ዓ/ም በቢሾፍቱ ከተማ ልዩ ስሙ አፋፍ ሃይቅ ዳርቻ የችግኝ ተከላ አካሄደዋል፡፡
በችግኝ ተከላው ዕለት በመገኘት ንግግር ያደረጉት የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ኮማንዳንት ኮሎኔል ዶ/ር ተገኝ ደጀኔ ሲሆኑ የአረንጓዴ አሻራው ተፈጥሮን የምናክምበት እና የሀገራችን ኢትዮጲያን ገፅታ ለመቀየር የሚደረግ መርሃ ግብር በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጲያዊ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል በማለት ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በችግኝ ተከላው ላይ የተሳተፉት በመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ስር የሚገኙ የኢንጅነሪንግ ኮሌጅ፤ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ߹የሪሶርስ ማኔጅመንት ኮሌጅ߹የምርምር ተቋም߹የዩኒቨርሲቲ ስታፍ አባላት߹የዩኒቨርሲቲ ሲቪል ማህበረሰብ እንዲሁም የ93ኛ ክ/ጦር 6ኛ ሻለቃ የሰራዊት አባላት ሁሉም በጋራ በመሆን በመርሃ ግብሩ ላይ በመሳተፍ እና አሻራውን በማስቀመጥ ችግኝ ተክሎ መሄድ ብቻ ሳይሆን መንከባከብም ስለሚያስፈልግ እንደ ሀገር ትኩረት በመስጠት ልንከባከብ ይገባል በማለት በተመሳሳይ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
መረጃዉ ከመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንዶክትሬኔሽን ዳይሬክቶሬት