በመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጅነሪንግ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለብዙ ጊዜ አገልግሎት ሳይሰጡ የቆዩ ሰፋፊ የእርሻ ቦታዎችን በማልማት ወደ ስራ ለማስገባትና ወቅቱን የጠበቀ ጥቅም እንድሰጡ እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት በመከላከያ ዩኒቨርሲቲ የኢንጅነሪንግ ኮሌጅ የእንስሳት እና እርሻ አስተባባሪ መ/አ ተሾመ አበራ ናቸው፡፡
በኮሌጁ ያሉ ከፍተኛ ጥቅም መስጠት የሚችሉ ነገርግን ሳንጠቀምባቸው የቀረነውን የእርሻ ቦታዎች ለማልማት አቅዴን ከመስራት ባለፈ ሰፊ ንቅናቄ በመፍጠር ጥቅም ላይ ለማዋል እየሰራን ነው በማለት ተናግረዋል፡፡
የእርሻ ማስፋፊያ ስራ ሲሠራ አብረው በመስራታቸው ኢኮኖሚያዊእናማህበራዊ ተጠቃሚ መሆናቸውን በወቅቱ በስራው ላይ ተሰማርተው የስራ እድል ተጠቃሚ የሆኑ የአካባቢው ወጣቶች ተናግረዋል፡፡
በሰኢድ አሊ
አማኑኤል ታደሰ
ፎቶ ግራፈር