የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ዋነኛ ከሆኑት ተግባራቶች መካከል የተማሩና በዕውቀት የበለፀጉ የተማሩ ወታደር ሙያተኞችን ማፍራት ሲሆን በዚህም እየተዋጉ ለሰራዊታችን ህክምና የሚሰጡ የጤና ሙያተኞችን፤ እየተዋጉ መሳሪያ የሚያመርቱና የሚጠግኑ መሐንዲሶችን፤ እየተዋጉ የሰራዊቱና የሐገር ሐብትን በአግባቡ የሚንከባከቡና የሚጠብቁ ፕሮፌሽናል ወታደር ሙያተኞችን በስልጠናና በትምህርት እንዲበቁ ማስቻል ነው፡፡
ዩኒቨርሲቲው የመከላከያ ሚኒሲቴር የጣለበትን ሐገራዊ ኃላፊነት መወጣት ያስችለው ዘንድ በለውጠ ሂደት ውስጥ ገብቶ ሥራዎችን በጥብቅ ክትትልና ወታደራዊ ዲሲፐሊን እየሰራ ይገኛል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በስሩ ከሚገኙ ኢንጅነሪንግ ኮሌጅ፣ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ ሪሶርስ ማኔጅመንት ኮሌጅና የምርምርና ልማት ኢንስቲቲዩትን በማስተባበር “ጤናማ ማህበረሰብ ለተቋማዊ ለውጥ“ በሚል ርዕስ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በሙሉ የአካል ብቃትና ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል። በ 07/09/2015 ዓ.ም በተጀመረው የስፖርት እንቅስቃሴ ላይ የዩኒቨርሲቲው ኮማንዳንት፡ በዩኒቨርሲቲው ሥር የሚተዳደሩ ተቋማት ኮማንዳንቶችና ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኮማንዳንት ብ/ጄነራል ከበደ ራጋሳ ዩኒቨርስቲው በለውጥ ሂደት ላይ መሆኑ፡ ለዚህም በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ በመግለጽ ስልጠናው የተሳካ እና ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም የሰራዊት አባላትና የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
በተጨማሪም በመማር ማስተማርና በመደበኛ ቢሮ ሥራዎች ላይ ሰራዊቱን ይበልጥ ፕሮፌሽናል ወተደር ሙያተኛ ሆኖ እንዲወጣና ይበልጥ ውጤታማ ለመሆን የአካል ብቃትና ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ጉልህ ሚና እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም የስልጠናው ዓላማ የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሸል በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያለውን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን የበለጠ በማሳለጥ የተቋሙን ራዕይ እውን እንዲሆን የለውጡ ቆስቋሽ መሆን እንዳለበትም ገልጸዋል። በመርሃ ግብሩ መሠረት ስልጠናው ከ07/09/2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 07/11/2015 ዓ.ም ድረስ የሚቀጥል ሲሆን ስልጠና በዋናነት የሚያተኩረው:-
ሥራን በዕቅድ መምራትና ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማረጋገጥ ያለው ሚና፣
የስራ ቦታ ተፈላጊ ክህሎቶች እና ጥራት ያለው የአገልግሎት አሰጣጥ፣
የአስተዳደር ሠራተኞች የስራ ተነሳሽነትና ውጤታማነት፣ እንቅፋቶችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች እና
ለዲሰፕሊን ተገዢ የሆኑ፡ ሥራቸውን የሚያከብሩ፤ ንቁና ቀልጣፋ የሆኑ ወታደር ሙያተኞችንና ሲቪል የዩኒቨርሲቲ አባላትን ማፍራት ናቸው፡፡
ከስፖርት እንቅስቃሴው ተሳታፊዎች መካከል አስተያየት ጠይቀናቸው ከሰጡን ምላሽ እንደተረዳነው እየተሰጠ ያለው ስልጠና ያለው ፋይዳ ለተቋሙ ብቻም ሳይሆን ለግል ህይወታቸውና ለጤንነታቸው አንዲሁም የከፍተኛ አመራር ጥበብን በመቅሰም የዩኒቨርሲቲውን ለውጥ ለማቀጣጠልና ለማስቀጠል ከፍተኛ አቅም እንደሚፈጥርላቸው በአስተያየታቸው ገልፀውልናል፡፡
ም/መ/አ ሰኢድ አሊ
መሰ/ወ/ር አማኑኤል ታደሰ
ፎቶግራፈሮች